Blog

በክልሉ በአንድ ቢሊየን ብር የፍሳሽ መስመር እና የማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ለማከናወን ውል ተፈረመ

ሀረር፣ ሀምሌ 8/2017(ሀክመኮ):-በሀረር ከተማ በአንድ ቢሊየን ብር የፍሳሽ መስመር እና የማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ለማከናወን ውል ተፈረመ።

ውሉን የፈረሙት የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አህመድ መሀመድ በአንድ ቢሊየን ብር ተግባራዊ የሚደረገው ፕሮጀክቱ 7 መቶ ሚሊየን ብሩ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስተር በኩል ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚሸፈን ሲሆን ቀሪው ብር በክልሉ መንግስት የሚሸፈን መሆኑንም ጠቁሟል።  

ፕሮጀክቱ በከተማው ብሎም በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ከፍሳሽ መስመሮች ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ጠቁሟል። በፕሮጀክቱ ከ14 ኪሎ ሜትር በላይ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ዝርጋታ የሚከናወን ሲሆን በቀን 1 ሺ 400 ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የማጣሪያ ጣቢያ እንደሚኖረውም ገልፀዋል። ፕሮጀክቱ ፍሳሹ በሚወገድባቸው አካባቢዎች የሚደርሰውን ተፅኖ ወደ ጥቅም በመቀየር መልሶ ግልጋሎት ላይ እንዲውል የሚያስችል መሆኑን ጠቁሟል። በዚህም መሰረት ፍሳሹ ተጣርቶ በአካባቢው ለመስኖ ልማትና ማዳበሪያነት እንዲውል የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ የሐረር ከተማን በኮሪደር ልማት ስራ ስማርት ሲቲ በማድረግ የከተሜነት ህይወትን ይበልጥ ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ከፍተኛ አበርክቶ እንደሚኖረውም ጠቁሟል። ፕሮጀክቱ በ 5 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ መሆኑም ተመላክቷል።

የተሰጡ አስተያየቶች

Comments