የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከደንበኞች ፎረም አባላት ጋር ውይይት አደረገ

ውይይቱ የተጀመረው በቅርቡ የባለስልጣን መ/ቤታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት ከኢንጂነር አህመድ መሐመድ ጋር ትውውቅ ከተደረገ ብኋላ ሲሆን ኢንጂነር አህመድ የደንበኞች ፎረም ለመ/ቤታችን አገልግሎት መሻሻል ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የደንበኞችን ፎረም ከአቋቋመ ብኋላ የተሻለ አሰራር እንዲፈጠር ለመ/ቤቱ አቅም ሆኖታል በማለት የተናገሩት ኢንጂነር አህመድ የደንበኞች ፎረም ከቀድሞ በተሻለ መልኩ ለመ/ቤቱ ከፍተኛ ሚና እንዲኖራቸው ህጋዊ ሰውነት እንዲኖራቸው ስራዎች የተሰራ ሲሆን በቀጣይም ስራቸውን በተሰጣቸው የህግ ሰውነት አማካኝነት እንዲሰሩ ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡
በሲስተም ዙሪያ ያለውን መሻሻሎች ለፎረም አባላት ያስረዱ ሲሆን ከዚህ ጋር የሚስተዋሉ ጊዜያዊ ቅሬታዎች መ/ቤቱ ፈትሾ ያስተካክላል በ2018 ዓ.ም ከሲስተም ጋር ተያይዞ ሰፊ ስራዎችንም እንደሚሰራ አብራረተዋል፡፡
መ/ቤቱ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሰፋፊ ስራዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እያከናወነ ነው ያሉት ኢንጂነር አህመድ መ/ቤታችን የኮሪደር ልማቱ በሚሰራባቸው ቦታዎች በሙሉ 24 ሰአት እየሰራ እና የውሃ ፈረቃ መዛባት ሲከሰት ቶሎ በፍጥነት ለመፍታት ከፍተኛ ርብርብ እያደገ እና ለደንበኞች ፍታሃዊ የውሃ ስርጭት እንዲኖር እየሰራ ነው በማለት አብራርተዋል፡፡
ኢንጂነር አህመድ የደንበኞች ፎረም አባላት ለመ/ቤቱ ራዕኢና ተልዕኮ መሳካት የአንበሳውን ድርሻ የሚጫወቱ የህዝብ ክንፎቻችን በመሆናችሁ በጋራ በዕቅድ ይበልጥ የምንሰራ መሆኑን ለመግለፅ እፈልጋለው በማለት ድጋፍም እንደሚያደረጉ ተናግረው መ/ቤቱ በቀጣይ በጀት አመት በ2018 ዓ.ም ለአሰበው የውሃ ውዝፍ ሂሳብ ክፍያ የማስከፈል ስራ፣ ፍታሃዊ የውሃ ስርጭት እንዲሁም የደንበኞችን የውሃና ፍሳሽ ቅሬታዎችን ለመቀነስ በጋራ በመተባበር ግልፅነትን በመፍጠር ስራዎችን መስራት አለብን በማለት ከአደራም ጭምር ያሳሰቡ ሲሆን የህዝብ ቅሬታ ወይም መልካም አስተዳደር ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አንዳንድ ባለሙያዎችን የማጋለጥ ስራም ከፎረም አባላቱ እንደሚጠበቅና በመ/ቤቱ በኩል እነዚህ ጥቆማዎችን ተቀብሎ አስፈላጊውን የአስተዳደር እርምጃ እንደሚወስድ በአፅኖት ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የደንበኞች አገልግሎት ዋና ስራ ሂደት አቶ አብዱሰመድ አብዱረህማን ከውሃ ክፍያ ጋር ተያይዞ ከደንበኞች ፎረም አባላት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄና አስተያየት በሰጡት ምላሽ አንድ የውሃ ደንበኛ በየወሩ የቆጣሪ ኪራይ ብቻ እንዳይከፍል ይልቁንም በወሩ የተጠቀመውን መረጃ በመያዝ በየወሩ ትክክለኛ የውሃ ክፍያን ሊከፍል ይገባል ያሉት አቶ አብዱሰመድ ደንበኛው በዚህ መልኩ ክፍያ በየወሩ የማይፈፅም ከሆነ አሁን ላይ ከበፊቱ ቫት ተጨምሮ ለከፍተኛ ክፍያ ጥያቄ ይጋለጣል በማለት አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም አቶ አብዱሰመድ ደንበኞች ለከፍተኛ ክፍያ እንዳይጋለጡ የሁሉም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ያሉ ሲሆን የፎረም አባላትም በተለያዩ ዘዴዎች ግንዛቤ መፍጠር ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
