Blog

የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለዋናው መ/ቤት የባለ 5 ወለል ህንፃ ግንባታ



የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለዋናው መ/ቤት የባለ 5 ወለል ህንፃ ግንባታ የመጀመሪያ ዙር ስራ ለማከናወን ከሙሉጌታ ዋለጌ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ጋር የውል ስምምነት በማድረግ ስራ አስጀምረዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለሠራተኞቹና ለደንበኞቹ ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር በዋናው መስሪያ ቤቱ የሚሰጠውን አገልግሎቶች ይበልጥ ለማቀላጠፍ ብሎም መ/ቤቱ ምንም እንኳን በራሱ ገቢ እንዲተዳደር በአዋጅ ቢቋቋምም በዋነኝነት ለደንበኞች ከሚያቀርበው እና ከሚፈለገው የውሃ አቅርቦት አለመመጣጠን የተነሳ በየጊዜው በሚሰበሰበው ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዲፈጥር ሆኖ የቆየ ሲሆን ይህንንም በቀጣይ በመቅረፍ ቢያንስ በሚያስገኘው ገቢ የአገልግሎት ወጪዎችን ቀስ በቀስ በመሸፈን ከክልል መንግሥት ድጎማ እንዲላቀቅ በማሰብ ይህንን የባለ 5 ወለል ህንፃ ግንባታ የመጀመሪያ ዙር ስራ በ120 ሚሊዮን ብር ለአሸነፊው ሰራ ተቋራጭ ለሙሉጌታ ዋለጌ ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ የሳይት ርክክብ አድርጓል።

ባለስልጣኑ ይህንን የህንፃ ግንባታ ለማስጀመር መጋቢት 5/2017 ዓ.ም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ አማካኝነት በቅጥር ጊቢ ውስጥ የመሰረት ድንጋይ እንዲያኖሩ ያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የተሰጡ አስተያየቶች

Comments