Blog

የገጠር ነዋሪዎችን የውሀ ሽፋን የሚያሳድግ በ34.7 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ቧንቧ ግንባታን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ መረቁ። 



ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የገጠሩ ነዋሪዎች የውሀ ሽፋን የሚያሳድጉ በ34.7 ሚሊዮን ብር ወጪ 15ሺ በላይ ህብረተሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ 6 የገጠር ቧንቧ ግንባታንም መርቀዋል። 

የሀረሪ ክልል ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ለሚያስገነባው ባለ 5 ወለል ህንፃ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።  ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅቱ እንደገለፁት ግንባታው መንግስት በውሀው ዘርፍ የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ይደጉማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።  ይህም ባለስልጣኑ በገቢ እራሱን እንዲችል አቅም የሚፈጥር እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አክለዋል ። 

ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል ።  በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት  ስራዎችን ዋጋ፣ጥራት እና ጊዜ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።  የባለሥልጣኑ ሀላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን እንደገለፁት ግንባታው በ120 ሚሊየን ብር የሚገነባ  ባለ 5 ወለል ህንፃ መሆኑን ጠቁመዋል ።  ይህም የስራ ከባቢን ምቹ በማድረግ የተገልጋይን እርካታ ለማረጋገጥ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል አብራርተዋል ። 

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የገጠር ነዋሪዎች የውሀ ሽፋን የሚያሳድጉ በ34.7 ሚሊዮን ብር ወጪ 15ሺ በላይ ህብረተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 6 የገጠር ቧንቧ ግንባታ መርቀዋል።  ፕሮጀክቶቹ የገጠር ነዋሪዎች የውሃ ሽፋን ለማሻሻል ከክልሉ መንግስት ፣ከተለያዩ ግብረሰናይ ፕሮግራም በተገኘ በጀት ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ በማዋል ከ14 በላይ አዳዲስ የገጠር የቧንቧ ግንባታ አካል መሆኑ ተጠቁሟል ።  በዛሬው እለትም በሁለቱ የገጠር ወረዳ ሶፊ እና ኤረር የተከናወኑት የልማት ስራዎች በርዕሰ መስተዳድሩ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁ ሲሆን በወቅቱም የማእድ ማጋራት መርሃግብር አከናውነዋል ። 

የተሰጡ አስተያየቶች

Comments